EthiopiaPoliticsRegionsSocial

አዴፓ እና አዴኃን ተዋሀዱ

አርትስ 03/ 03/2011

 

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ዛሬ ውህደት መፍጠራቸውን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አዴፓ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ወደ በረሀ ወርዶ የታገለላቸው ሀሳቦች አዴፓም አቋም ይዞ የሚታገለው ሀሳብነው፤ስለሆነም ሁለቱ ድርጅቶች መዋሃዳቸው ለአንድ ዓላማ መቆማቸውን ያሳያል ብሏል፡፡

የአማራ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበዉ ከዛሬ ጀምሮም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ውህደት ፈጥረናል ብለዋል፡፡

አዴኃን በቅርቡ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በሰላም ለመታገል ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ድርጅት ነዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button