Breaking News

መንግስትና ኦነግ አብሮ ለመስራት ተሰማሙ

መንግስትና ኦነግ አብሮ ለመስራት ተሰማሙ

አርትስ 05/03/2011

በነ አቶ ዳዉድ ኢብሳ የሚመራው  ኦነግ፤ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ከፌደራል መንግስት ጋር ተስማምቶና ተደማምጦ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዛሬ ከመንግስት ጋራ በጋራ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ለሃገር እድገትና አንድነት ከንግዲህ ተደማምጦ መስራት ግድ ይለናል ብለዋል፡፡

በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ በመስራት እንቀጥላለን ያሉት የኦነግ ሊቀመምበር አቶ ዳዉድ ኢብሳ፤ በቀሩት ጉዳዮች በሂደት እየተመካከርን እየተስማማን እንሄዳለን ብለዋል፡፡

በዚህም ካሁን በኋላ የ ኦነግ ና የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሰላማዊ መንገድ ከመንግስት ጋር አንድ ሆነን ለመስራት ተሰማምተናል ብለዋል

leave a reply