Breaking News

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አብዱልከሪም መሀመድ የ2010 ዓ/ም ኮከብ ተጫዋች ሆነ

የቅዱስ ጊዮርጊሱ አብዱልከሪም መሀመድ የ2010 ዓ/ም ኮከብ ተጫዋች ሆነ

አርስ ስፖርት 06/03/2011

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2010 ዓ/ም የኮከቦች ሽልማት ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

ፌዴሬሽኑ የሽልማት ስነ ስርዓቱን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ፣ የከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ እናሁለተኛ ዲቪዚዮን፣ ከ17 እና ከ20 አመት በታች ውድድሮች ላይ በኮከብነት፣ በአሸናፊነት እና በምስጉንነትለተሸለሙ ክለቦች፣ ተጫዋቾችና ዳኞች እውቅና ሰጥቷል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ፤ አሸናፊዎቹ በተቋቋመ ቴክኒካል ኮሚቴ፣ ዳኞችና ታዛቤዎችኮሚቴ እንዲሁም ሌሎች አካላት እንደተመዘኑ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በወንዶች ፕሪምየር ሊግ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አብዱልከሪም መሀመድ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ተብሏል፤  ገብረመደህን ኃይሌ ኮከብ አሰልጣኝ፤ የጅማ አባ ጅፋሩ ግብ ጠባቂ ዳንየል አጃዬ ኮከብ ተጫዋች እና ኦኪኪ አፎላቢኮከብ ግብ አግቢ ተብለዋል፡፡

በሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን ሰናይት ቦጋለ ኮከብ ተጫዋች፣ ኤልያስ አብርሃም ኮከብ አሰልጣኝ፣ ሎዛ አበራ ኮከብ ግብአስቆጣሪ በመሆን ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

በምስጉን ዳኞች ዘርፍ በወንዶች፤ በፕሪምየር ሊጉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሃን እና ረዳት ኢንተርናሽናልዳኛ ተመስገን ሳሙኤል፤ በሴቶች አንደኛ ዲቪዚዮን ደግሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ ፀሀይነሽ አበበ እና ረዳትኢንተርናሽናል ዳኛ ወይንሸት አበራ  አሸናፊ ሁነዋል፡፡

በስፖርታዊ ጨዋነት ዘርፍ በክለቦች ጥረት ኮርፖሬት፣ የአዳማ ሴቶችና ጅማ አባ ጅፋር፤ በተጫዋቾች የመከላከያውፍፁም ገብረማርያም እውቅና ተሰጥቷል፡፡

leave a reply