AfricaHealth

የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞቹን ከምስራቃዊ ኮንጎ አሸሸ

የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞቹን ከምስራቃዊ ኮንጎ አሸሸ

 

አርትስ 10/03/2011

 

የድርጅቱ ሰራተኞች የኢቮላ ወረረሽኝ በተስፋፋባት ቤኒ በሽተኞችን እየረዱ በነበሩበት ወቅት በአማፂያንና በሰላም አስከባሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ነው አካባቢውን ለቀው የወጡት፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የጤና ባለሞያዎቹ የሚኖሩበት ህንጻ በተኩስ ልውውጡ ወቅት  በመሳሪያ ተመቷል፡፡

ሰራተኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም የዓለም ጤና ድርጅት በቤኒ ግዛት የኢቮላ ወረርሽን ከተከሰተ ወዲህ የስጋቱ መጠን በማየሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና ባለሞያቹን ለማሸሽ ተገዷል ፡፡

የዲሞክራቲክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በግጭቱ ምክንያት ኢቮላን የመከላከሉ ተግባር በመስተጓጎሉ የበርካቶች ህይዎች አደጋ ላይ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ስድስት የማላዊ ዜግነት ያላቸው የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአማፂዎቹ መገደላቸው ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button