EconomyEthiopia

ኢትዮጵያ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ከምንግዜውም በላይ አመቺ ሃገር ሆናለች ተባለ

አርትስ 10/03/2011

 

ይህንን ያሉት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍጹም አረጋ ናቸው። አቶ ፍጹም ዛሬ ከእንግሊዝና ከሌሎች ሃገራት ለተውጣጡ 40 የሚደርሱ የታላላቅ ኩባንያ ባለቤቶችና ተወካዮች ስለወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታና ስለአመቺ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም ካለፉት ሰባት ወራት ወዲህ በኢትዮጵያ ስለተካሄዱት አበይት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጦች ለባለሃብቶቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሃገሪቱ በስፋት የተገነቡትና ወደስራ የገቡት ግዙፍ የኢንደስትሪ ፓርኮች ኢትዮጵያን በማምረቻ ኢንደስትሪው ዘርፍ የታላላቅ ኩባንያዎች ዋና መናኸሪያ አድርገዋታል ነው ያሉት።

ሃገሪቱ እንደ አየር መንገድ  እና ቴሌኮም ያሉ ኩባንያዎችን በከፊል የግል ለማድረግ የጀመረችው እንቅስቃሴ ታዋቂ የዓለም ንግድ ተቋማትን እየሳበ መሆኑንም ተናግረዋል።

አቶ ፍጹም እንደተናገሩት ሃገሪቱ የምጽዋ ወደብን መጠቀም መጀመሯና በቅርቡም እድሳት ተደርጎለት ወደስራ የሚገባው የአሰብ ወደብ ለገቢና ወጪ ምርቶች ማጓጓዝ አመቺ አጋጣሚ ፈጥሯል።

ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሃገር ሆናለች ያሉት አቶ ፍጹም በጉብኝት ላይ ያሉት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መዋዕለንዋያቸውን በስራ ላይ እንዲያውሉም ጥሪ አቅርበዋል።

መንግስት ኩባንያዎቹ የሚፈልጉትን ማንኛውንም ድጋፍ ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኑንም ቃል ገብተዋል።

መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የፌየርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ዓለምአቀፍ ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በበኩላቸው ከነዚህ ኩባንያዎች ሃገሪቱ ግዙፍ ካፒታል እና የረቀቀ ቴክኖሊጂ እንዲሁም ኮርፖሬት አስተዳደር ጥቅም ታገኛለች ።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button