Breaking News

በህገ-ወጥ መንገድ ወደሃገር ውስጥ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

በህገ-ወጥ መንገድ ወደሃገር ውስጥ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

በህገ-ወጥ መንገድ ወደሃገር ውስጥ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ

አርትስ 12/03/2011

50 ክላሽንኮቭ እና አንድ ላውንቸር እና አርባ ካርታ ጥይት የጫነው መኪና ከአዲስ አበባ የተነሳ ሲሆን በቁጥጥር ስር የዋለው ደብረብርሃን ከተማ ላይ ነው።

የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢአለ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት እንዳስታወቁት መሳሪያዎቹ የተያዙት ከትናንት በስቲያ ምሽት ከሌሊቱ 7፡00 ላይ ነው ።

የጦር መሳሪያዎቹ በጋምቤላ በኩል የገቡ መሆኑ የተነገረ ሲሆን አሽከርካሪውም ከነህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሏል።

አሽከርካሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን የተናገሩት አቶ ካሳሁን ተጠርጣሪው የተያዘው ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ከሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደርና ጽጥታ ጉዳዮች መምሪያ ጋር በመተባበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

leave a reply