AfricaHealth

የስኳር ህመም መድሀኒት እጥረት የዓለማችን ስጋት ሆኗል

የስኳር ህመም መድሀኒት እጥረት የዓለማችን ስጋት ሆኗል

አርትስ 13/03/2011

በዓለም ላይ የስኳር ህመምተኞች ቁጥር ባልተጠበቀ ፍጥነት እያደገ ስለመሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

በቅርቡ የተደረገ ጥናት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2030 40 ሚሊዮን የስኳር ህመምተኞች የኢንሱሊን እጥረት ይገጥማቸዋል ይላል፡፡

ሲ ኤን ኤን የጥናት ውጤቱን ጠቅሶ እንደዘገበው ከ11 ዓመት በኋላ ኢንሱሊን የተባለው መድሀኒት የሚያስፈልጋቸው አዋቂዎች ቁጥር 79 ሚሊዮን ይደርሳል፡፡

በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ  የጥናት ቡድኑን የመሩት ረዳት ፕሮፌሰር ሳንጃይ ባሱ አሁን ላይ በተለይ በእስያና በአፍሪካ ሀገራት የኢንሱሊን አቅርቦትና ፍላጎት አይመጣጠንም ብለዋል፡፡

የመድሀኒቱ አቅርቦት የማይሻሻል ከሆነ የአፍሪካ የእስያና የኦሽኒያ ሀገራት በችግሩ በከፍተኛ ደረጃ ይጠቃል ሲሉም አጥኝዎቹ አስጠንቅቀዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ሰዎች የችግሩ ተጠቂ ላለመሆን የአኗኗር ዘይቤያቸውን መቀየር ግድ ይላቸዋል፡፡

ካልሆነ ግን የስኳር ህመም ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ እንቅስቃሴ አለመድረግና አመጋብን ካለማስተካከል የሚመጣ በመሆኑ ህመሙ ያለባቸውም ሆኑ የሌለባቸው ሰዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ይላሉ ባለሞያዎቹ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button