Breaking News

ሰሞኑን ወደ ባህርዳር ያቀኑት የሰላም አምባሳደር እናቶች ነገ መቀሌ ይሄዳሉ

ሰሞኑን ወደ ባህርዳር ያቀኑት የሰላም አምባሳደር እናቶች ነገ መቀሌ ይሄዳሉ

አርትስ 17/03/2011

“ሴቶች የሰላም ሐዋርያ ናቸው” በሚል መሪቃል ተጉዘው ዛሬም ባህርዳር ከተማ የሚገኙት እናቶች የሰላም እንቅስቃሴያቸውን ቀጥለዋል፡፡

ዜጎች ያለምንም ስጋት በሀገራቸው ተዘዋውረው ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲረጋገጥ ሰላም የሰው ልጆች መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ የሃይማኖት አባቶች የሰላም ዘብ መሆን አንደሚገባቸው  እናቶች ተናግረዋል። ከዘጠኙም ክልሎች የተውጣጡ የሰላም እናቶች በከተማዋ  በተካሄደው የወጣቶች መድረክ ላይ ተገኝተው  የወለድነውን ሰላም ልንንከባከበው ይገባል፣ ለዚህም ሁሉም ኢትዮጵያውያን የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡይገባቸዋል በማለት ወጣቶች ለሰላም እንዲቆሙ ተንበርክከው ተማፅነዋል፡፡  ሰላም ከሌለ ሀገር እንደሌለ በመረዳት ለሰላም ቀን ከሌሊት ሊታትሩ እንደሚገባ  አሳስበዋል፡፡

እናቶቹ በባህርዳር ቆይታቸው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ከክልሉ አፈ-ጉባኤ፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም ጉዳይ እንደሚወያዩ የሰላም ተናግረዋል። ይህ የእናቶች የመጀመሪያ ጉዞ  በሁሉም ክልሎች እንደሚደረግም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በነገው ዕለትም ይኸው ጉዞ ቀጥሎ እናቶቹ ወደ መቀሌ ያመራሉ ተብሏል፡፡

leave a reply