EthiopiaPolitics

ጋህዴን አዲስ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን መረጠ

 

ጋህዴን አዲስ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን መረጠ

አርትስ 16/02/2011

የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ኡሙድ ኡጅሉ ኢበቡና አንኳያ ጃክን የንቅናቄው ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።

ንቅናቄው አዲስ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር የመረጠው የቀድሞው የጋህዴን ሊቀመንበርና ምክትላቸው አቶ ጋትሏክ ቱትና አቶ ስናይ አኩዌር በፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ነው።

ሁለቱ አመራሮች ከድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ አባልነት ቢሰናበቱም በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ይቀጥላሉ ተብሏል።

አዲስ የተመረጡት የንቅናቄው ሊቀመንበር ጋህዴን የክልሉን ሰላምና ፀጥታ በማረጋገጥ ሰፊ የልማት ስራዎችን እንደሚያከናውን ለፋና ተናግረዋል።

ለዚህም የክልሉ ህዝብ ከድርጅታቸው ጎን እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button