Africa

ካይሮ ከዶሀ ጋር መቆራረጧ እንደጎዳት አመነች

አርትስ 19/03/2011

የግብፅ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅ አህመድ አብደል ሀገራቸው ከኳታር ጋር ባላባት የዲፕሎማሲ መቃቃር ሳቢያ ወደ ዶሃ በረራ ማቆመቀቸው ኪሳራ እንዳደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር ስራ አስኪያጁን ጠቅሶ እንደዘገበው የግፅ አየር መንገድ በሊቢያና በሶሪያ ያለው አለመረጋጋትም በገበያው ላይ ተፅእኖ አሳድሮበታል፡፡

የግብፅ አየር መንገድ በመንግስታቸው ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሌሎች አየር መንገዶች ጋር በዋጋ መወዳደር ሌላው ትልቁ ፈተና እንደሆነበትም ሀላፊው ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጅ ስራ አስካያጁ ኪሳራ ደረሰብን ማለት ወደቅን ማለት አይደለም፤ ዓለማችን ሰፊ ስለሆነች ሌሎች አማራጭ መዳረሻወችን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ግብፅ በፈረንጆቹ 2017 ከገልፍ አጋሮቿ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤሜረቶችና ከባህሬን ጋር በማበር በኳታር ላይ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ማእቀብ መጣሏ ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button