Breaking News

የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ ይገባሉ

የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ ይገባሉ

አርትስ 19/03/2011

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራሮች የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ግንባሩ አስታውቋል፡፡

የኦብነግ ቃል አቀባይ አቶ አዳኒ ሂርሙጌ በሰጡት መግለጫ ድርጅታቸው ላለፉት 34 ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን የትጥቅ ትግልለማቆም ከመንግስት ጋር ከስምምነት በመድረሱ ነው ጠቅልሎ ወደ አገር ቤት የሚገባው ብለዋል፡፡

ግንባሩ ትጥቁን በመፍታት አገራዊ ለውጡን በመደገፍ የበኩሉን ለማበርከት መዘጋጀቱንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ቅዳሜ የሚገቡት አመራሮች ለበርካታ ዓመታት ትጥቅ ትግል ላይ የነበሩ በመሆናቸው ህዝቡ እስካሁን ሲያደርግ እንደነበረውደማቅ አቀባበል እንዲያደርገላቸውም ቃል አቀባዩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የግንባሩ ወታደሮች ትጥቅ ፈትተው ወደ አገር መግባታቸው ይታወሳል፡፡

leave a reply