Africa

ማጉፉሊ የቻይናን እጅ መግፋት አይቻልም አሉ

አርትስ 19/03/2011

ከምእራባዊያን ተደጋጋሚ ማስፈሪያ የሚደርሳቸው የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የቻይና ድጋፍ  ተቀዳሚ ምርጫችን ነው ብለዋል፡፡

ምክንያታቸው ደግሞ ቻይና ብድርም ሆነ እርዳታ ስትፈቅድ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን አታበዛብንም የሚል ነው፡፡

“የቻይና መንግስት ሲደግፍህ ይደግፍሀል፤ ይህን አድርግ ፣ይህን ደግሞ አታድርግ በሚል የራሱን ፍላጎት አይጭንብህም” በማለት የቤጂንግን ድጋፍ ለምን እንደመረጡ አብራርተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዳሬሰላም ዩንቨርሲቲ በ96 ቢሊዮን የታንዛኒያ ሽልንግ ለሚገነባው ቤተ መጽሃፍት የቻይና መንግስት የ40.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጎላቸዋል፡፡

በአንፃሩ የዴንማርክ መንግስት  ባለፈው ወር የታንዛኒያ ፖሊሲ ግብረ ሶዶምን የሚቃወም በመሆኑ ምክንያት የ10 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መከልከሏን ለአብነት አንስተዋል ማጉፉሊ፡፡

በመሆኑም ታንዛኒያ ከቻይና ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር ተግተው እንደሚሰሩ ነው ፕሬዚዳንቱ የገለፁት

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button