Uncategorized

ሞስኮ ወደ ክሬሚያ ድንበር ዘመናዊ ሚሳኤሎችን ልታጓጉዝ ነው

አርትስ 20/03/2011

 

ሩሲያ ከዩክሬን ጋር አሰጥ አገባ ውስጥ መግባቷን ተከትሎ ኤስ 400 በተሰኘው ዘመናዊ ሚሳኤል የተደራጀ ጦሯን ልታስጠጋ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ሮይርተስ እደንደዘገበው ሩሲያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 ክሬሚያን ወደ ግዛቷ ካስገባች ጀምሮ  በየጊዜው ዘመኑ ያፈራቸውን ሚሳኤሎችን በአካባቢው ማከማቸቱን ተያይዛዋለች፡፡

የሩሲያ ደቡባዊ ወታደራዊ እዝ ቃል አቀባይ ቫዲም አስታፊየቭ (Vadim Astafyev) እንዳስታወቁት ኤስ 400 የተባለውን ዘመናዊ ሚሳኤል የታጠቀው ሻለቃ ጦር በፍጥነት ወደ ክሬሚያ ተንቀሰሳቅሶ ለግዳጅ ዝግጁ ይሆናል፡፡

ሩሲያ ወታደራዊ ሀይሏን በክሬሚያ ማከማቸት የረዥም ጊዜ እቅዷ ቢሆም አሁን ለዩክሬን መልእክት በማስተላለፍ ትክክለኛው ጊዜ ሆኖላታል ተብሏል፡፡

ክሪሜያ ውስጥ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚሸፍን ሚሳኤል ታግዘው ግዳጃቸውን መወጣት የሚችሉ አራት ሻለቃ የጦር ሰራዊት አባላት ጥቁር ባህርን በተጠንቀቅ እየጠበቁ  መሆኑም ተገልጿል፡፡

የሩሲያ  ክሪሜያ ሚሳኤሎችን ማስጠጋቷ ውጥረቱን ይበልጥ ያባብሰዋል በማለት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ቅሬታውን አሰምቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button