Breaking News

ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ከእስር ሊፈቱ ነው

ከሁለት ሺ በላይ የሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ሀገራት ከእስር ሊፈቱ ነው

አርትስ 20/03/2011

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳሳወቀው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናነት ሲሰራቸው ከሚገኙ ስራዎች አንዱ በውጭ ሃገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ደህንነት ማስጠበቅ ነዉ ይህንንም ስሰራ ነበር ብሏል፡፡

አሁን  በታንዛኒያ፤ የመን፤ሳውዲ አረቢያ ና የመን የሚገኙ 2000 የሚሆኑ ዜጎችን የማስፈታቱ ስራ መጀመሩንም የሚኒስቴሩ  ቃል አቀባዩ አቶ መለስ አለም ተናግረዋል፡፡

አቶ መለስ በመደበኛ መግለጫቸው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ አዳዲስ አምባሳደሮች ሹመት እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡ አምባሳደሮቹ ባልተለመደ ሁኔታ ምሁራንና የአካዳሚክ ባለሙያዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ይካተቱበታል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሚሲዮኖችና በዋና መስሪያ ቤት የሚገኙ ሰራተኞች ድልድልም በመስሪያ ቤቱ አዲስ የሪፎርም አሰራር መሰረት ተካሄዷል፡፡  አላስፈላጊ የዲፕሎማት ክምችት ያለባቸውን ኢምባሲዎችም ታይተዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአገሪቱ አንጋፋ መስሪያ ቤት ነው ስንል በምክንያት ነው ያሉት አቶ መለስ፤ ታዋቂና ታላላቅ ዲፕሎማቶችን ለሃገርና ለዓለም ያፈራ መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡ ኢምባሲዎችም የዜጎቻችን እንዲሆኑ ይሰራል ብለዋል፡፡

leave a reply