AfricaEthiopiaSport

በነገው ዕለት ከመቀሌ-አስመራ -ባጽእ ከተማ የብስከሌት ውድድር ይካሄዳል

አርትስ ስፖርት 20/03/2011

የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ከመቀሌ- አስመራ -ባፅእ ከተማ የሚዘልቀው የብስክሌት ውድድር ሲካሄድ፤በኢትዮጰያና በኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ታስቦ የሚካሄድ መሆኑንአስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ገነት አረፈ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት “ውድድሩ በህዝቦቹ መካከል የተጀመረውን የልማትናየንግድ ግንኙነት ያጠናክራል” ብለዋል ።

በውድድሩ ላይ የትግራይና የኤርትራን ምርጥ ብስክሌተኞች እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል። የትግራይ ክልል ስምንት ምርጥኮርሰኞችም በውድድሩ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡

ነገ ከመቀሌ የሚጀምረው ውድድር፤ ከመቀሌ- አስመራ 300 ኪሎ ሜትርና ከአስመራ- ባፅእ ከተማ 105 ኪሎሜትር ይሸፍናልተብሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button