Sports

ሉካ ሞድሪች የባላንዶር ባለክብር ሆኗል

ሉካ ሞድሪች የባላንዶር ባለክብር ሆኗል

አርትስ ስፖርት 25/03/2011

የ2018 የባላንዶር ሽልማት ትናንት ምሽት በፓሪስ ይፋ ሁኗል፡፡ በምሽቱ ከአስር አመታት በኋላ ከሮናልዶ እና ሜሲ ውጭ የባላንዶር ክብር የሪያል ማድሪዱና ክሮሽያ ተጫዋች ሉካ ሞድሪች በድምፅ ብልጫ አሸናፊ ሁኗል፤ ሞድሪች ይህ ሽልማት ባለፉት አስርት አመታት ክብሩ እየተገባቸው ላመለጣቸው ተጫዋቾች ዣቪ፣ ኢኒየስታ እና ሽናይደር መታሰቢያ ይሁንልኝ ብሏል፡፡

የአምናው ባለክብር ክርሲቲያኖ ሮናልዶ ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ የአትሌቲኮ ማድሪዱና ፈረንሳያዊው አንቱዋን ግሪዝማን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

ወጣቱ ክልያን ምባፔ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ሊዮኔል ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዓመታት በኋላ ከሶስቱ ውጭ የሆነ ሲሆን አምስተኛ ደረጃ ላይ ተገኝቷል፡፡ ሞሀመድ ሳላህ፣ ራፋኤል ቫራን፣ ኤደን ሀዛርድ፣ ኬቨን ዲ ብሯይኔ እና ሃሪ ኬን እስከ አስር ያለውን ደረጃ ተቆናጥጠዋል፡፡

በሴቶች የሊዮኗ እና የኖርዌይ ተጫዋች አዳ ሀገርበርግ የዘንድሮውን ባላንዶር አንስታለች፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ በተሰናዳው ከ21 ዓመት በታች የሚገኙ ኮከብ ወጣቶች ሽልማት KOPA TROPHY ደግሞ ክልያን ምባፔ አሸናፊ ሁኗል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button