Africa

ግብ ፃ ዊቷ አክትረስ ከባህል አፈነገጥሽ ተብላ ቅጣት ሊጣልባት ነው

ግብ ፃ ዊቷ አክትረስ ከባህል አፈነገጥሽ ተብላ ቅጣት ሊጣልባት ነው

አርትስ 25/03/2011

ራኒያ ዩሱፍ የተባለቸው ግብፃዊት የፊልምና የፋሽን ባለሞያ ባለፈው ሳምንት ካይሮ ላይ በተካሄደው የፊልም ፌስቲቫል ላይ ከማህበረሰቡ ወግ በወጣ አለባበስ መድረክ በመውጣቷ  ነው  ቁጣ የበረከተባት፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በካይሮ የሚገኙ በርካታ የህግ ባለሞያዎች በተዋናይዋ ላይ ክስ ለመመስረት በየፊናቸው ተዘጋጅተዋል፡፡

ዩሱፍ በካይሮ ተቃውሞ የገጠማት በመድረክ ላይ በተገኘችበት ወቅት ሰውነቷን  የሚያጋልጥ ልብስ ለብሳ በመታየቷ ነው፡፡

ተዋናይዋ ግን እኔ ማንንም የሚያስከፋ ድርጊት ፈፅሜያለሁ ብዬ አላስብም ይህን ዓይነት አለባበስም የለበስኩት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ብላለች፡፡

ዩሱፍ በመጭው ጥር ወር ፍርድ ቤት እንድትቀርብ ቀጠሮ የተያዘላት ሲሆን እስከ አምስት ዓመት የእስር ቅጣት ይጠብቃታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button