Breaking News

አምስት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አምስት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አምስት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አርትስ /26/03/2011
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን አምስት የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

ኢቢሲ እንደዘገበዉ የፌደራል ፖሊስ ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት ባካሄደው ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ኦፕሬሽን አምስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮችን በቁጥጥር ስር አውሏል።

የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊና የቀድሞ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚገኙበት ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በሰኔ 17ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት እንዲሁም በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች አከባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የችግሩ ጠንሳሾች ሆነው የተጠረጠሩ ናቸው ብሏል ፌደራል ፖሊስ።

ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ግብረ ሀይሉ አስታውቋል።

leave a reply