EthiopiaPolitics

የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

አርትስ 27/03/2011

የኦስትሪያው መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሰባስቲያን ከርዝ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በተለያዩ በጋራ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚወያዩ ይጠበቃል። መራሄ መንግስት ሰባስቲያን ከርዝ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በጀርመን በርሊን በተካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተገናኝተው ነበር። በተገናኙበት ወቅትም የሁለትዮሽ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን፥ ሀገራቱ የጋራ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር በትብብር እንደሚሰሩ መስማማታቸው የሚታወስ ነው ፡፡ መረጃው የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button