Uncategorized

የየመን ተዋጊ ሀይሎች ለሰላም ውይይት ወደ ስዊድን ተጉዘዋል

የየመን ተዋጊ ሀይሎች ለሰላም ውይይት ወደ ስዊድን ተጉዘዋል

አርትስ 27/03/2011

 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስተባባሪነት ስቶኮልም ላይ የሚካሄደው የሁለቱ ወገኖች የሰላም ውይይት በብዙዎቹ ዘንድ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

የድርጅቱ ልዩ ልዑክ ማርቲን ግሪፊትዝ ተዋጊ ሀይሎቹን ለማደራደር በቦታው ተገኝተዋል፡፡ በተቀናቃኝ ሀይሎቹ መካከል ለዓመታት የተፈጠረው አለመተማመን ድርድሩን ከባድ ያደርገዋል የሚል ስጋት ፈጥሯል ፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው በተዋጊ ሀይሎቹ መካከል ቀጥተኛ ውይይት አይደረግም፡፡ ይልቁንም ሁለቱም ሀሳባቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አደራዳሪ ቡድን አማካይነት ያስተላልፋሉ ነው የተባለው፡፡

አሁን ላይ በየመን የሚካሄደውን የርስበርስ ጦርነት በእጅ አዙር የሚመሩት በምእራባዊያን የምትታገዘው ሳውዲ አረቢያና በሌላኛው ጫፍ የቆመችው ኢራን ስለመሆናቸው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱን የሚያካሂዱት አካላት በዚህ መልኩ ተገናኝተው ለመነጋገር መስማማታቸው በራሱ ስኬት ነው ይላሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለየመን ዜጎች የሸቀጥ ዕቃወችና የእርዳታ ቁሳቁሶች የሚገባባት የሁዴይዳ ወደብ ከጦርነት ነፃ እንድትሆን በተደጋጋሚ ቢያሳስብም ብዙም ውጤታማ አልነበረም ፡፡

የአሁኑ ውይይትም እነዚህንና በሀገሪቱ እየደረሰ ያለውን የህይወትና የንብረት ጥፋት ለማስቆም ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button