AfricaEducationEthiopia

ተማሪ መና ተስፋዬና ቤተልሄም ጥበቡ ‹‹የሒሳብ ንግስት›› ሆነው ተመረጡ

ተማሪ መና ተስፋዬና ቤተልሄም ጥበቡ ‹‹የሒሳብ ንግስት›› ሆነው ተመረጡ

አርትስ/28/03/2011
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ የአፍሪካ የሒሳብ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በጋራ ያዘጋጁት ‹‹ሴቶች በሒሳብ ሳይንስ ዘርፍ እንዲሰማሩ መሳብ›› በሚል ርዕስ ሲካሄድ የነበረው አውደ ጥናት ተጠናቋል፡፡
አውድ ጥናቱ ከአዲስ አበባ 1ኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሒሳብ እውቀት የተወዳደሩ ሴት ተማሪዎችን በመሸለም እና የሒሳብ ንግስትን በመምረጥ ነው የተጠናቀቀው፡፡
የ8ኛ ክፍል ተማሪዋ መና ተስፋዬ ከአለም ብርሃን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዋ ቤተልሄም ጥበቡ ከቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ‹‹የሒሳብ ንግስት›› በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የፕሮግራሙ አስተባባሪ  ዶክተር ይርጋለም ፀጋዬ የተማሪዎቹ መሸለም ሌሎች ሴት ተማሪዎች በሂሳብ ትምህርት ዘርፍ እንዲሳቡና የወደፊት ሳይንቲስትነት ህልም እንዲኖራቸው ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡

መረጃዉን ያገኘነዉ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button