Ethiopia

በሳዑዲ እስር ላይ ያሉ 2400 ኢትዮጵያውያን ሊፈቱ ነው

በሳዑዲ እስር ላይ ያሉ 2400 ኢትዮጵያውያን ሊፈቱ ነው

አርትስ 01/04/11

ሚኒስቴሩ  በተለያዩ አገሮች ለእስር ተዳርገው እንዲሁም ደህንነታቸው ለአደጋ ተጋልጦ የቆዩ ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ጥረት እያደረገ ነው፡፡

በዚህም መሰረት ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በተደረገ ማግባባት እና ድርድር በያዝነው ሳምንት 2400 ዜጎቻችን ከእስር በምህረት ተፈተው ወደ አገራቸው የሚመለሱ ይሆናል፡፡

የሳዑዲ አረብያ ህግ በማይፈቅድ ተግባራት ላይ በመሳተፋቸው ተይዘው በጂዛንና አስር ማረሚያ ቤቶች  ውስጥ ከነበሩት ውስጥ አራት መቶ ሃምሳ የሚሆኑት ዛሬ  እና ቀሪዎቹ አራት መቶሃምሳ ደግሞ በመጪወ አርብ  ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት ህይወታቸውን ለአደጋ ባጋለጠ ሁኔታ ቀይ ባህርን አቋርጠው ሳዑዲ አረቢያ የገቡ 1500 ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት ለመመለስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳዑዲ አረቢያ ጂዳ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቆንስላ ጽ/ቤት በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ እየደረገ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዜጎችን መብት ለማስከበር እና ህይወት ለመታደግ በጄዳና አከባቢዋ በተለያዩ ወንጀል የታሰሩ እንዲፈቱ፣ የረዥም ጊዜ ፍርድ የተበየነባቸው በምህረት እንዲለቀቁ ወይም ወደ እናት አገራቸው ተመልሰው የእስር ጊዜያቸውን እንዲጨርሱ ግፊት እያደረግኩ ነዉ  ሲል አስታውቋል ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button