Uncategorized

ሲ ኤን ኤን ባለ ቅን ልቦና ያለውን ዶክተር የዓለሚቱ ጀግና አድርጎ መረጠ

ሲ ኤን ኤን ባለ ቅን ልቦና ያለውን ዶክተር የዓለሚቱ ጀግና አድርጎ መረጠ

አርትስ 01/04/11

ዶክተር ሪካርዶ ፑን ቾንግ ችግረኞችን ለመታደግ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

በተለይ ፔሩ ውስጥ ከገጠር ወደ ከተማ ተፈናቅለው የእለት ጉርስም ሆነ ለጎናቸው ማረፊያ የሌላቸውን ህፃናት ጉድለታቸውን ለመሙላት ሌት ተቀን ለፍተዋል፡፡

እነዚህን ህፃናት ጤናቸውን በመጠበቅ፣ ስነ ልቦናቸው ጠንካራ አእንዲሆንና የተሟላ ስብዕና ይዘው እንዲያድጉ ላደረጉት ጥረት ሲ ኤን ኤን የዓመቱ ጀግና በሚል የ100 ሺህ ዶላር ተሸላሚ አድርጓቸዋል፡፡

እሳቸው ግን ጀግናው እኔ ሳልሆን እነዚህ ህፃናት ናቸው፤ ከነሱ ጋር ውሎ ማደር ያለውን የመንፈስ እርካታ እኔ ብቻ ነኝ የምረዳው ብለዋል፡፡

ለዶክተር ፑን ቾንግ  ሀኪም መሆን በሽተኞችን ማከም ቀዳሚው እንጂ የመጨረሻ ግብ አይደለም፡፡ ትልቁ ስራ ቤተሰቦቻውን መንከባከብ ጭምር ነው፡፡

ፑን ቾንግ ቤት አልባና አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ህፃናት የሚረዳ ግብረ ሰናይ ድርጅት በማቋቋም እስካሁን ከ8 ሺህ በላይ ህፃናት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡

ዶክተሩ ለዚህ በጎ ተግባር ያነሳሳቸው በአንድ ወቅት የፔሩ ዋና ከተማ ሊማ ውስጥ የሆስፒታል በረንዳ ላይ የተኙ ችግረኞችን በማየታቸው ነው፡፡

ለነዚህ ሰዎች አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብለው የተነሱት ዶክተር ፑን ቾንግ ለህፃናቱ የህይዎት ክህሎት ለወላጆቻቸው ደግሞ የጤና አጠባበቅ ስልጠናዎችን በመስጠት የበርካቶችን ህይወት ቀይረዋል፡፡

ሽልማቱ በተሰጣቸው ገንዘብ ተጨማሪ መጠለያወችን በመገንባት የህፃናቱን ህይወት ይበልጥ ቀላል ለማድረግ መዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button