EthiopiaRegionsSocial

ለለውጥ እና ለነውጥ ተጋላጭ የሆነውን እንቅስቃሴ ወደለውጥ እንዲያመዝን ልንሰራ ይገባል አሉ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት

ለለውጥ እና ለነውጥ ተጋላጭ የሆነውን እንቅስቃሴ ወደለውጥ እንዲያመዝን ልንሰራ ይገባል አሉ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት

አርትስ 02/04/2011

ከፌደራልና ከክልል የጸጥታ አካላት ጋር በወቅታዊ ሃገራዊ የጸጥታና የለውጥ ስራዎች ላይ የተዘጋጀ የጋራ የምክክር መድረክ  የሰላም  ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በተገኙበት ከትናንት ጀምሮ    በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የጸጥታ አካላት ሰላም ለማስከበርና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ማህበራዊ አቅሞችን ማዕከል ያደረገ ስራ ሊያከናውኑ እንደሚገባ ያሳሰቡት የሰላም ሚኒስቴሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ለውጡን ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች የታየው የሰላም መደፍረስ አገሪቱ ላይ ችግር እያስከተለ ነው ብለዋል ።

”በአንድ በኩል ለለውጥ በሌላ በኩል ለነውጥ ተጋላጭ መሆኑ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ አጠናክሮ በመቀጠል ሚዛኑ ለለውጥ ያደላ እንዲሆን በትጋት ልንሰራ ይገባል” ብለዋል።

በዚህ ሀገር አቀፍ የጸጥታ ተቋማት የውይይት የክልልና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የሁሉም የክልል የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱም አገር አቀፍ የጸጥታና የሪፎርም ስራዎች አስመልክቶ የ 5 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በሁሉም ክልሎች ቀርቦ ዛሬም  ውይይት እንደሚካሄድበት ታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button