EconomyEthiopiaRegions

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፊታችን እሁድ ይመረቃል

አርትስ 02/04/2011

 

ኢንዱስትሪ ፓርኩ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራልና ክልል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተጋባዥ እንግዶች በሚገኙበት እንደሚመረቅምተገልጿል።

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እያስገነባቸው ከሚገኙት ስድስት ትልልቅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል ከሁሉም ግዙፉ ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ገደንሰር በሚባለው አካባቢ 4 ቢሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ ነው የተገነበዋው።

ፓርኩ በአጠቃላይ 4 ሺህ 185 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን፥ የፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በ150 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው።

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ 15 ሼዶች ያሉት ሲሆን፥ ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።

በኢንዱስትሪ ፓርኩ በሚገነቡት ሼዶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ውጤቶች ማምረቻዎች፣ በኮንስትራክሽን፣ በወረቀትና በአልባሳት ዘርፍ የተሰማሩ ዓለም አቀፍኩባንያዎች እንደሚገቡም ይጠበቃል።

የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ CCECC በተባለ የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን፥ ኩባንያው ከዚህ ቀደም በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ፕሮጀክትና በኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ሥራዎች ላይየተሳተፈ ነው።

ኤፍ ቢ ሲ

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button