Ethiopia

ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ገንዘብ ያዝኩ አለ። ንብረቱና ገንዘቡ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ተገምቷል።

ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ገንዘብ ያዝኩ አለ። ንብረቱና ገንዘቡ ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ተገምቷል።

ጽህፈት ቤቱ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በህዳር ወር ብቻ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች የያዘ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድኃኒት፣ ምግብ ነክ፣ አልባሳት፣ መዋቢያ እቃዎች ፣ ልባሽ ጨርቅና ጫማዎች ይገኙበታል።

የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የትምህርት እና ቡድን አስተባባሪ ሄለን ዓባይነህ እንደገለጹት ከዚህ በተጨማሪም የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሲጋራና የትምባሆ ውጤቶች፣ ስስ ፌስታል፣ የቤት መገልገያ፣ የጽሕፈት እና የህንጻ መሳሪያ በኮንትሮባንድ ሊገባ ሲል ተይዟል።በጥሬ ገንዘብም 201 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ስር ውሏል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥር በሚገኙት ቶጎ ጫሌ፣ ተፈሪ በር፣ ሐርሽን፣ ለፈኢሳ እና አውበሬ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተያዙ መሆኑም ተገልጿል።

ህገ-ወጥ ደርጊትን ለመከላከል መንግሥት ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ መሆኑን የገለጸው ገቢዎች ሚኒስቴር ህዝቡም ህገወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button