AfricaEthiopia

ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኘ

አርትስ 04/04/2011

 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 28  ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ገቢው የተገኘው ከሰኔ 2010 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2011 . ባሉት አምስት ወራቶች ውስጥ ነው፡፡

ጅቡቲ ከ17 ሚሊየን  ዶላር በላይ የኃይል ግዥ በመፈፀም ከፍተኛውን ድርሻ የምትወስድ ሲሆን ቀሪው  ደግሞ ከሱዳን የተገኘ ነው፡፡

ኢትዮጵያ 2010 በጀት ዓመት ለሱዳንና ጅቡቲ ካከናወነችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 75 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

ሃገሪቱ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል በማልማት በምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር በስፋት እየሰራች ሲሆን ለጅቡቲና ሱዳን በዓመት በአማካኝ 150 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በመሸጥ ላይ እንደምትገኝ ቢሮው ገልጻል፡፡

ሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ካላት እምቅ አቅም ለመጠቀምና የሁለትዮሽ የኃይል ትስስር ግንኙነት ለመጀመር ፍላጎት ከማሳየት ባሻገር ወደ ስምምነት እየመጡ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል እንዳገኘነዉ መረጃ ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከሶማሌ ላንድ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠር የሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button