EthiopiaRegions

የአማራ እና ቅማንት ማህበረሰቦች የሰላምና የእርቅ ጉባኤ ተካሄደ

የአማራ እና ቅማንት ማህበረሰቦች የሰላምና የእርቅ ጉባኤ ተካሄደ

አርትስ 05/04/2011

ህዝባዊ የሰላምና የእርቅ ጉባዔው በአማራ እና ቅማንት ማህበረሰቦች መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት መፍትሄ ለመስጠት የተከናወነ ሲሆን የተካሄደውም በጎንደር ከተማ ነው።

የጉባኤው ዓላማ በክልሉ በተለይ በማዕከላዊና ሰሜን ጎንደር ዞኖች የተከሰቱ ማንነትን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለዘለቄታው መፍታት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በመድረኩ ባደረጉት ንግግር የሁለቱም ማህበረሰብ ህዝብ ተዋልዶ አብሮ የኖረ መሆኑን ገልጸው ህዝብና ታሪክ ግን በዘመናት መካከል ይቀጥላሉ ብለዋል።

ስለሆነም በሚያልፍ የመሪነት ዘመናችን የማያልፍ የታሪክ ጠባሳ እንዳንተው ልንጠነቀቅ ይገባል ነው ያሉት አቶ ደመቀ።

ግጭት ለታላቅ ሃገር እና ተስፋ ለሰነቀ ህዝብ አይመጥንም ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ልታከብረን እና ልናከብራት የምንችላት ሃገር ለመገንባት በህግ የበላይነት ልንገዛ ይገባል ብለዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በአማራ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ከተከሰቱት ግጭቶች ጋር ተያይዞ 30 ሺህ የሚደርሱ ተፈናቀዮች መኖራቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ላቀ አያሌው ገልፀዋል፡፡ ዜናው የአማራ ብዘሁን መገናኛ ነው።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button