World News

ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ:: ዩ ኤስ ኤድ የተሰኘው የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ለኮቪድ 19 ምላሽ እና ማገገሚያ የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ማፅደቁ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር እንደገለፁት በጀቱ የኮቪድ 19 ስርጭትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመግታት ያለመ ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም በጀቱ በተለያዩ ሀገራት በቫይረሱ ሳቢያ የተከሰተውን የኢኮኖሚ ችግር ለማነቃቀት እንደሚያስችል ነው የገለጹት፡፡ አሁን ላይ ክትባት ባልተዳረሰባቸው ሀገራት በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ እና ወረርሽኙን ለመግታት አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ከእርዳታው 445 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ ከሰሃራ በታች ለሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚከፋፈል ፋና ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button