EthiopiaPoliticsRegions

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌን ሊቀመንበር በማድረግ ተጠናቀቀ

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌን ሊቀመንበር በማድረግ ተጠናቀቀ

አርትስ 10/04 /2011

 4ኛው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሴቶች ሊግ በመቀሌ ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትነው የተጠናቀቀው።

በጉባኤው ማጠቃለያ  ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ ወይዘሮ መስከረም አበበ ደግሞ ምክትል ሆነው መመረጣቸው ታውቋል።

115 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ አዲስ ሊቀመንበር የመረጠው የቀድሞዋ ሊቀመንበር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የሥራ ጊዜ በመጠናቀቁ ነው ።

አዲሷ ተመራጭ ወይዘሮ መሰረት መስቀሌ ባደረጉት ንግግርም በስራ ዘመናቸው ለሰላም መስፈን፣ ለሴቶች ተጠቃሚነት ፣ ለአገር አንድነት እና ለህዝቦች መቀራረብ እሰራለሁ ብለዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button