Sport

በመጨረሻም የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ኦሌ ጉናር ሶልሻየር አዲሱ የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሁኗል

በመጨረሻም የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ኦሌ ጉናር ሶልሻየር አዲሱ የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሁኗል

አርትስ ስፖርት 10/04/2011

ኦሌ ጉናር ሶልሻየር የአሰልጣኝ ዦዜ ሞሪንሆን ስንብት ተከትሎ ክለቡን እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ እንደሚያሰልጥኑ ክለቡ አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ የቀድሞ አሰልጣኝ ማይክ ፊላን ደግሞ ሶልሻየር ምክትል አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

ክለቡ የሶልሻየርን ቅጥር ትናንት ምሽት በስህተት በድረ ገፁ ያሰፈረ ቢሆንም ወዲያውኑ ከገፁ ሰርዟል፤ ከዚያ በኋላ በመገናኛ ብዙሃኑ የሶልሻየርን ወደ  ቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ዳግም መምጣት በሰፊው ሲዘገብ ነበር፡፡

የዩናይትድን  የድረ ገፅ የሹመት ብስራት ተከትሎ የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስተር ኢርና ሶልበርግ በማህበራዊ ሚዲያ ‹‹ለኖርዌይ እግር ኳስ ታላቅ ቀን ነው፤ ቀያይ ሰይጣኖቹን በደንብ ያዛቸው፣ መልካም ዕድል›› ብለውት ነበር ወዲያውኑ ግን እርሳቸውም ፅሁፉን አጥፍተውታል፡፡

የቀድሞው ኖርዌያዊ ተጫዋች ኦሌ ጉናር ሶልሻየር በዩናይትድ ከ1996 እስከ 2007 ድረስ የተጫወተ ሲሆን በ11 የውድድር ዓመት ለክለቡ 126 ጎሎችን አበርክቷል፡፡

የ45 ዓመቱ ሶልሻየር የኖርዌዩን ሞልዴ ክለብ ሲያሰለጥን የነበረ ሲሆን በሞልዴ ሁለተኛ የአሰልጣኝነት ጊዜውን እስከ አዲሱ ሹመት ድረስ አሳልፏል፤ በዚህ የፈረንጆቹ ታህሳስ ወር መጀመሪያ አዲስ ኮንትራት የ2018 የውድድር ዓመት አጠናቋል፤ በመጭው መጋቢት ወር ላይ ደግሞ ይጀመራል ተብሏል፡፡

ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዥ ስድስተኛ ላይ ይገኛል፤ ሶልሻየርስ እውን ሞሪንሆ እምቢ ያላቸውን ስኬት ወደ ቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ይመልስ ይሆን…

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button