Ethiopia

በጅግጅጋ ከ41 ሺህ በላይ ዶላር ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙ ተገለፀ

በጅግጅጋ ከ41 ሺህ በላይ ዶላር ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙ ተገለፀ

አርትስ 11/04/2011

እንደ ገቢዎች ሚኒስቴር ገለፃ 41 ሺህ 693 የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች በጅግጅጋ ቅርንጫፍ አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውለዋል ፡፡

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በቶጎ ጫሌ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው፡፡

አቶ ደመላሽ መንግሥት ህገ-ወጥ ደርጊቶችን ለመከላከል  ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሮ እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ህዝቡም እያደረገ ላለዉ ንቁ ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ህገወጦችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ሃላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም ኃላፊው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button