EducationEthiopiaPoliticsSocial

አመራሮቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመቀነስ መስራት አለብን አሉ

አርትስ 12/04/2011

 

በመቀሌ ፣ አዳማ ፣ አምቦና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንደተናገሩት  የትምህርት አመራሮቹ በተቋማቱ የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘለቄታዊነት ለመቀነስ በጥናት ላይ የተመሰረተ የተቀናጀ ስራ መስራት ተገቢ ነው።

ተማሪዎቹ የራሳቸው የህይወት መስመር ኖሯቸው አላማቸውን ከግብ የሚያደርሱበት አቅም እንዲኖራቸው የትምህርትተቋማቱ በጥናት ላይ የተመሰረተ ቅንጅታዊ አሰራር መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል አመራሮቹ ።

በትምህርት ተቋማት የሚፈጠሩ አስተዳደራዊና ውጫዊ የግጭት መንስኤዎች ተለይተው መፈታት እንደሚኖርባቸውምአመልክተዋል።

አመራሮቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግጭት መነሻ ምክንያቶች፣ የቅድመ ግጭት መከላከል ስልቶችና ድህረ ግጭትመፍትሄዎች ጥናት በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባም ተናግረዋል ብሏል ኢዜአ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button