AfricaPolitics

የኮንጎ ተቃዋሚዎች ምርጫው ዳግም ቢራዘም ለሚከተለው ችግር ተጠያቂዎች አይደለንም አሉ

የኮንጎ ተቃዋሚዎች ምርጫው ዳግም ቢራዘም ለሚከተለው ችግር ተጠያቂዎች አይደለንም አሉ

አርትስ 16/04/2011

ፕዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ የማይሳተፉበት የዲሞክራቲክ ኮንጎ ምርጫ ከተያዘለት ቀነ ቀጠሮ በአንድ ሳምንት መራዘሙ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ደጋፊወቻቸውን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡

ባለፈው እሁድ ሊካሄድ የነበረው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተራዘመው የምርጫ ቁሳቁሶች የተከማቹበት መጋዘን በመቃጠሉ እና መሳሪያወቹ በመውደማቸው ነው ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ይህን ምክንያት አይቀበሉትም፡፡ የካቢላ አስተዳደር ምጫውን ያራዘመው ሆን ብሎ አንዳች ተንኮል ለመስራት ነው ብለው ያምናሉ፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ደጋፊዎች የምርጫውን መራዘም ዜና በሰሙ ቅፅበት ጎዳናዎችን በአመፅ በማጥለቅለቅ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡

የፓርቲ አመራሮቹለአንድ ሳምንት የተራዘመው ምርጫ  አሁንም ዳግም የሚራዘም ከሆነ የኛን ትእዛዝ ሳትጠብቁ መብታችሁን ለማስከበር እንዳታመነቱ ብለዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ተቃዋሚወቹን ያሳሰባቸው ዋናው ነገር የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በኤሌክትሮኒክ በመታገዝ  የድምፅ አሰጣጡን ሂደት አከናውናለሁ ማለቱ ነው፡፡

የአሜሪካ መንግስት የካቶሊክ ቤተ ክስቲያን እንዲሁም በሀገሪቱ የሚገኙ አክቲቪስቶች  የተቃዋሚ ፓርቲወቹን ስጋት ይጋሩታል፡፡

ምክንታቸው ደግሞ ይህን ማሽን መጠቀም ያስፈለገው የተቃዋሚወችን ድምፅ ለመንጠቅ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነው የሚል ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button