Ethiopia

የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 5/ 2011 አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በእርቀ-ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ነው ረቂቁን ያጸደቀው፡፡

የኮሚሽኑ ዓላማም በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ሰላም፣ ፍትህ፣ ብሄራዊ አንድነትና መግባባት፣ እንዲሁም እርቅ እንዲሰፍን መስራት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቂም ስሜቶችን ለማከም ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ ተጠቅሷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button