Breaking News

ሁለቱ ኮሪያዎች በባቡር የመገናኘታቸው ነገር እውን ሊሆን ጫፍ ላይ ደርሷል

ሁለቱ ኮሪያዎች በባቡር የመገናኘታቸው ነገር እውን ሊሆን ጫፍ ላይ ደርሷል

ሁለቱ ኮሪያዎች በባቡር የመገናኘታቸው ነገር እውን ሊሆን ጫፍ ላይ ደርሷል

አርትስ 17/04/11

ዛሬ ማለዳ ላይ ከደቡብ ኮሪያ ሴኡል የተነሱ 100 ልኡካን በሰሜን ኮሪያ ድንበር ወደምትገኘው ኬይሶንግ ከተማ  አቅንተዋል፡፡

የጉዟቸው ዓላማ ደግሞ ሴኡልና ፒዮንግያንግ በጋራ በሚዘረጉት የባቡር መስመር ፕሮጀክት የስምምነት ስነ ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው፡፡

የደቡብ ኮሪያ የውህደት ሚኒስቴር እንዳለው በስነ ስርዓቱ ላይ ከሩሲያ፣ ከቻይና፣ እንዲሁም ከሞንጎሊያ የተወከሉ ባለ ስልጣናትና በሴኡል የሚገኙ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ይታደማሉ፡፡

እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ1950 እስከ 1953 ከተዋጉ በኋላ ለዘመናት ተለያይተው የኖሩት ሁለቱ ኮሪያዎች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እርስበርሳቸው በጠላት ዓይን ሲተያዩ ነበር የኖሩት፡፡

አሁን ግን በተለይ ሰላም ወዳድ በሆኑት በደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃይ ኢን ተናሽነት የተጀመረው ወዳጅነታቸው ፍሬ ማፍራት ጀምሯል፡፡

leave a reply