Breaking News

የ2019 እግር ኳሳዊ ትንበያዎች

Goal.com ባወጣው መረጃ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት (2019) ለፈፀሙ የሚችሉ 10 ግምታዊ እግር ኳሳዊ መረጃዎችን አስፍሯል፡፡

 

Goal.com ባወጣው መረጃ በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት (2019) ለፈፀሙ የሚችሉ 10 ግምታዊ እግር ኳሳዊ መረጃዎችን አስፍሯል፡፡

በ2019 የአፍሪካ ዋንጫ፣ ኮፓ አሜሪካ፣ የሴቶች ዓለም ዋንጫ እና ሌሎች ሁነቶች በመጪዎቹ 12 ወራት ይጠበቃሉ፡፡

1ኛ፡ ዩቬንቱስ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ሊያሸንፍ ይችላል

ክለቡ እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ያስፈረሙበት ሂደት ለክብሩ ትልቅ ፍላጎት ስላላቸው ነውና የዚህ ዓመት ዋንጫ ወደ ጣሊያን ምድር ሊያመራ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

2ኛ፡ ዦዜ ሞሪንሆ ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው ዳግም ሊመለሱ ይችላሉ

ሪያል ማድሪድን ሳንቲያጎ ሶላሪ እየመሩት ይገኛሉ፤ በቋሚነት ደግሞ ከማንችስተር ዩናይትድ ከተሰናበቱ በኋላ ያለ ስራ የሚገኙት ዦዜ ሞሪንሆ  ወደ ስፔን አቅንተው ሊረከቡ ይችላሉ

3ኛ፡ አንቶኒዮ ኮንቴ ማንችስተርን ሊረከቡ እንደሚችሉ ተነግሯል

ጣሊያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ አሁን ያለው የውድድር ዓመት ሲጠናቀቅ ከኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ሊረከቡ ይችላሉ

4ኛ፡ የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን የሴቶች ዓለም ዋንጫን ሊያሸንፉ ይችላል

ውድድሩ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን በ2015 አሸናፊ የሆነው የአሜሪካ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በተከታታይ ሊያነሳ ይችላል

5ኛ፡ እግሊዛውያን አሰልጣኞች በፕሪምየር ሊጉ በሊጉ እየተመናመኑ ይሄዳሉ

6ኛ፡ ፒ.ኤስ.ጂ በፋይናንስ አወጣጥ ቀውስ ምክንያት ከቅጣት ለማምለጥ ሲል ክዋክብቶቹን ሊያጣ ይችላል

7ኛ፡ ሊዮኔል ሜሲ ወደ ባላን ዶር ክብር በድጋሜ ይመለሳል

8ኛ፡ እንግሊዝ የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ዋንጫን ታነሳለች

9ኛ፡ ብራዚል እና ኔይማር የኮፓ አሜሪካን ክብር ይቀዳጃሉ

10ኛ፡ የርገን ክሎፕ በመጭው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን የሚያሸንፉ ከሆነ የሊቨርፑልን የፕሪምየር ሊግ ጥማት ሊያርሱ ይችላሉ

የእርስዎስ ግምት ምን ይሆን… ? ሀሳብዎን ይንገሩን ..?

leave a reply