EthiopiaLegal

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገው ክትትል 3 መትረየስ እና በርከታ ጥይቶች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡ የህዝቡ ተሳትፈትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪያውን አስተላልፏል፡፡
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ A- 59022 በሆነ ቶዮታ ፒካ አፕ ተሽከርካሪ በባለሙያ ተፈትተው ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዙ የነበረ ሦስት መትረየስ ፣ 1924 የስታር እና 1856 የማካሮቭ በድምሩ 3780 የሽጉጥ ጥይቶች ከ37 የጥይት መያዥ ጥር 18 ቀን 2011 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አዲሱ ገበያ አከባቢ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በመተባበር ከህዝብ የደረሳቸውን መረጃ መሰረት በማድረግ ባከናወኑት ተግባር በቁጥር ስር አውለዋል፡፡
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመግታት ተግባሩ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽኑ ገልፆ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመከለካል እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ቀና ትብብር መልካም ስለሆነ በይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል ።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button