EthiopiaSportSports

ኢትዮጵያ ቡና በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ተሸነፈ

ኢትዮጵያ ቡና በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ ተሸነፈተሸነፈ

የ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር ስድስት ጨዋታዎች በአዲስ አበባ እና ክልል ስታዲየሞች ላይ ተካሂደዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲም የደቡቡን ደቡብ ፖሊስ አስተናግዶ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ በሊጉ ሁለተኛ ድሉን እንዲያሳካ ምክንያት የሆኑትን ጎሎች ዘሪሁን አንሼቦ እና ዮናስ በርታ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡
ለቡና አጥቂው አቡበከር ናስር ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ወደ ጨዋታ ቢመልስም ከሽንፈት ግን ሊታደገው አልቻለም፡፡ ቡናማዎቹ ከአቡበከር ጎል በኋላ ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር በተደጋጋሚ ያደረጉት ጥረት አልተሳካላቸውም፡፡
ክልል ስታዲየሞች ላይ በተመሳሳይ 9፡00 ላይ በተከናወኑ ግጥሚያዎች ደግሞ፤ ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ ደደቢትን የገጠመው ሲዳማ ቡና 3 ለ 0 በመርታት የነጥቡን መጠን ከፍ አድርጓል፡፡
መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በትግራይ ስታዲየም መከላከያን አስተናግዶ 5 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት በ23 ነጥቦች ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ማሳደግ ችሏል፡፡ ስሑል ሽረ በትግራይ ደርቢ ሜዳው ላይ በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ 1 ለ 0 ተረትቷል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር ጅማ ላይ ከባህር ዳር ከነማ እንዲሁም አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ያደረጉት ግጥሚያ በተመሳሳይ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
ነገ በዕለተ ዕሁድ ሁለት ጨዋታዎች ሲከናወኑ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ በሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ መካከል 10 ፡00 ሲል ይከናወናል፡፡
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ኢንተርናሽናል አርቢትር ብሩክ የማነ ብርሐን ይመሩታል ተብሏል፤ ቀን 9፡00 ሲል ሀዋሳ ከነማ በሃዋሳ ሰው ሰራሽ ስታዲየም ከድሬዳዋ ከነማ ጋር ይፋለማል፡፡
የነገውን ጨዋታ ጨምሮ ሁለት ያላደረጋቸው ጨዋታዎች ያሉት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ12 ጨዋታዎች ላይ በሰበሰባቸው 24 ነጥቦች ሊጉን እየመራ ይገኛል፤ ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች ያሉት መቐለ በ11 ጨዋታዎች 23 ነጥቦችን ይዞ ሁለተኛ እንዲሁም ሲዳማ ቡና በተመሳሳይ 23 ነጥቦች በግብ ክፍያ አንሶ ሶስተኛ እና ሁሉንም የሊግ ግጥሚያዎች ያከናወነው ኢትዮጵያ ቡና በ22 ነጥብ አራተኛ ደራጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
መከላከያ ሁለት ቀሪ ጨዋታ እያለው በ10 ነጥቦች፣ ደቡብ ፖሊስ ሁሉንም ጨዋታዎች አድርጎ በ8 እና ደደቢት ሁለት ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ4 ነጥቦች ወራጅ ቀጠና ውስጥ ተገኝተዋል፡፡
የመከላከያው ምንይሉ ወንድሙ በ9 ጎሎች ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው፤ አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመቐለ፣ አዲስ ግደይ ከሲዳማ፣ ታፈሰ ሰለሞን ከሀዋሳ እና ዳዋ ሆቴሳ ከአዳማ በዕኩል 8 ጎሎች ይከተላሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button