Politics

“ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ግለሰቦችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን ኅብረተሰቡ ጆሮ ሊሰጣቸው አይገባም” ተባለ

ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ግለሰቦችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን ኅብረተሰቡ ጆሮ ሊሰጣቸው አይገባም ሲሉ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ተናገሩ።

 

አፈ-ጉባኤዋ ይህን የተናገሩት የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ በክልሉ የሰላም እና ደኅንነት ቢሮ የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።

በውይይቱ በክልሉ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖችና አካባቢው በማንነት ሽፋን የተቀሰቀሱ ግጭቶች የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የተጀመሩ ምክክሮች እና ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ጉባኤው በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት የሰው ሕይወት እና ንብረት በጠፉበትና ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው በተፈናቀሉበት ወቅት የሚደረግ መሆኑን የገለጹት አፈጉባኤዋ ሰላም እንዳይሰፍን የሚያደርጉ ግለሰቦችንና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድኖችን ኅብረተሰቡ እንዳይከተላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button