Uncategorized

በሁለት ቀናት ዉስጥ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ 5.2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ተያዘ

ታህሳስ 21/2011 ዓ.ም መነሻዉን ዱባይ ያደረገዉ  አቶ ቴዎድሮስ በርሄ ከቀኑ 4 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በጉምሩክ ኮሚሽን በቦሌ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች በተደረገ አካላዊ ፍተሻ መንገደኛዉ በለበሰዉ የዉስጥ ሱሪ 3.2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተገኔ ደረሰ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይም ታህሳስ 22/2011 ዓ.ም ከዱባይ የተነሳዉ ተጓዥ አቶ ሰላሙ ደረጀም ቦሌ አለም አቀፍ ኤሪፖርት ከሌሊቱ 4 ሰዓት ሲደርስ በጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ አካላዊ ፍተሻ ግለሰቡ 2 ኪ.ግ የብር ጌጣጌጥ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡

በሁለት ቀናት የተያዘዉ አጠቃላይ የብር ጌጣጌጥ 5.2 ኪ.ግ ሲሆን ግምታዊ ዋጋዉም 312 ሺ ብር መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል፣ የኮንትሮባንድ ንግድ በሀገር ላይ የሚያስከትለዉን ጉዳት በመገንዘብ ኮንትሮባንዲስቶች ከዚህ ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ እና በቅ/ፅ/ቤቱ ያለዉ ክትትል እና ቁጥጥርም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል፡፡ መረጃዉን ያገኘነዉ ከገቢዎች ሚኒስቴር ነዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button