Uncategorized

ፕሬዝዳንት ሺ በታይዋን የመጣብንን አንታገሰውም አሉ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሽ ጂንፒንግ ታይዋን የቻይና አካል መሆኗን ታሪክም ህግም ይደግፈናል፣ ከአንድ ቻይና ፖሊሲያችን አንድ ጋት አናፈግፍግም ብለዋል፡፡

ሺ ይህን ያሉት ቻይና ከታይዋን ጋር የምታደርገውን ጦርነት አቁማ በሰላም የመዋሀድ ሀሳብ ያቀረበችበትን 40ኛ ዓመት በምታከብርበት ወቅት ነው፡፡

አንዲት ጠንካራ ቻይና ሳይሆን ሁለት ቻይናዎች እንዲኖሩ የሚያሴሩትን ሁሉ አጥብቀን እንቃወማለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ ታይዋንን የቻይና አካል ለማድረግ ሁሉንም የእርምጃ አማራጮች እንወሰወዳለን ብለዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ነገሮች በሰላም የማይቋጩ ከሆነ የፕሬዝዳንት ሽ ጂንፒንግ አስተዳደር የመጨረሻ አማራጩ ታይዋንን በሀይል ማስመለስ ነው፡፡

እስከዛሬ ታይዋን ራሷን ችላ ሀገር እንድትሆን የሚደረገውን ጥረት ሁሉ በማክሸፍ ብዙ ስኬቶችን አስመዝግበናል አሁንም ይህች ደሴት የቻይና አካል ስለመሆኗ የሚጠራጠር ካለ እሱ ተሳስቷል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ ፡፡

የታይዋኗ ፕሬዝዳንት ፃይ ኢንግ ዌን በበኩላቸው ቻይና የ23 ሚሊዮን ህዝብ ፍላጎት እና በነፃነት የመኖር መብት ልታከብር ይገባል በማለት ቻይናን ወቅሰዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ግን ሰላማዊ ድርድር ውጤት ካላመጣ ጦርነት ወስጥ ለመግባት የምንገደድበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም የሚል ንግግር አድርገዋል፡፡

በተለይ በውስጥ ጉዳያችን እየገቡ የአንድ ቻይና ፖሊሲያችንን የሚፈታተን ድርጊት የሚፈፅሙ ወገኖች እጃቸውን መሰብሰብ አለባቸው ሲሉም ጠንካራ የማስጠንቀቂያ መልእክ አስተላልፈዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button