EthiopiaPolitics

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለዋወጥ መሆኑን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይለዋወጥ መሆኑን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጹ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይን ዛሬ በጽ/ቤታቸው ሲቀበሉ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት የጊዜ ፈተናዎችን ያለፈና በሁኔታዎቸ መለዋወጥ የማይቀያየር መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ወርቅነህ ባደረጉት ንግግር ቻይና የምትከተለውን ወጥና በሌላ አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት እንዲሁም የዜጎችን ህይወት የሚለውጥ ድጋፍ የማድረግ ፖሊሲን አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ላለት ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ ጠቅሰው፣ ያላቸውን ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂያዊ የትብብር አጋርነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ በመንግስት የሚተዳደሩ ኩባንያዎችን በከፊል ወይም በሙሉ ወደግል ለማዞር መወሰኗን ገልጸው በዚህም የቻይና መንግስትና የግል ኩባንያዎችን ቢሳተፉ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ግንኙነትና ተጠቃሚነት እንደሚያጠናክር እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡ በቤጂንግ በተካሄደው የቻይና አፍሪካ ፎረም ፕሬዝዳን ሺ ጂ ፒንግ በአፍሪካ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ይፋ ያደረጉትን የ60 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፋይናንስ ድጋፍ አድንቀው፣ ኢትዮጵያ የሚጠበቅባትን ለመወጣት ትሰራለችም ብለዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ቻይና ያላቸውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት አድንቀው ኢትዮጵያ እምነት የሚጣልበት አጋር በመሆኗ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ለውጥ ምክንያት በቻይና በኩል የሚደረግ ምንም ዓይነት የፖሊሲ ለውጥ የለም ብለዋል። ይልቁንም ግንኙነቱ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣ ይበልጥ ለማሳድግም ይስራል ብለዋል። የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ሁሉን አቀፍ፣ ታሪካዊና የማይናወጥ ነውም ብለዋል። ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ ትቀጥላለቸ በማለት ገልጸዋል።

ምንጭ:- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button