መምህራን ሰላምና ሃገር ወዳድ ዜጋ የመፍጠር ትልቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገለፀ
የሰላም ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከመምህራን ማህበር ጋር በመተባበር ትልቅ ሃገራዊ ጉባኤ እና የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል ::
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የሰላም ሚኒስትሯን ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች አካላትም ተገኝተዋል::
ሰላምና ሃገር ወዳድ መምህራኖች ሰላምና ሃገር ወዳድ ተማሪዎችን ያፈራሉ በሚል መሪ ቃል ነው ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው::
መምህራን ለሃገር ሰላም ዘብ መቆም አለባቸውም ተብሏል::
ከሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ መምህራኖች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡