Breaking News

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፋሲል ከነማ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅሏል

ፋሲል በሩብ ፍፃሜው ከአዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከነማ አሸናፊ ጋር ይጫወታል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ዋንጫ ፋሲል ከነማ ወደ ሩብ ፍፃሜው ተቀላቅሏል

በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ (የኢትዮጵያ ዋንጫ) ጨዋታ የመጀመሪያ ዙር ግጥሚያ በትግራይ ስታዲየም፤ በወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ፋሲል ከነማ መካከል ተካሂዶ እንግዳው ፋሲል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ዐጼዎቹን ወደ ሩብ ፍፃሜው ያሻገረች ግብ ያሬድ ባየህ (ገብርዬ) በ52ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ ይህን ተከትሎ የጎንደሩ ቡድን በቀጣይ በሩብ ፍፃሜው ከአዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከነማ አሸናፊ ጋር ይጫወታል ተብሏል።

ሁለቱ ቡድኖች በገና በዓል ዋዜማ በፕሪምየር ሊጉ ተገናኝተው ያለግብ በአቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

በአንደኛው ዙር ስሑል ሽረ ከ ሲዳማ ቡና 2 ለ 2 አቻ ተለያይተው የሽሬው ቡድን በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት አሸንፏል፤ መከላከያ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍፃሜውን አስቀድመው ተቀላቅለዋል፡፡

በዙሩ ድሬዳዋ ከነማ ከ ሀዋሳ ከነማ፣ ወላይታ ድቻ ከ ጅማ አባ ጅፋር፣ አዳማ ከተማ ከ ባህር ዳር ከነማ፣ መቖለ 70 እንደርታ ከ ደቡብ ፖሊስ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት ወደፊት ይፋ በሚደረጉ ቀኖች የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

leave a reply