Breaking News

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ ታውቋል።

13 ጨዋታዎች በቀጣይ ጊዜያት የሚደረጉ ይሆናል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታዎች መቼ እንደሚደረጉ ታውቋል።

በ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በተለያዩ ሳምንታትና ምክንያቶች ሳይከናወኑ የቀሩ በርካታ ግጥሚያዎች አሉ፡፡ ወደ ፊትም የጅማ አባ ጅፋርን የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎ ተከትሎ የማይካሄዱትን ሁለት ጨዋታዎች ጨምሮ 13 ጨዋታዎች በቀጣይ ጊዜያት የሚደረጉ ይሆናል ተብሏል።

እነዚህ ጨዋታዎችም መቼ እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

የሊጉ አንደኛ ዙር መደበኛ መርሐ ግብር የካቲት 4 ቢጠናቀቅም የተስተካካዮቹ ጨዋታዎች እስከ የካቲት መጨረሻ ድረስ ይደረጋል።

በዚህም ጥር 8 ፋሲል ከነማ ከ ደደቢት፤ ጥር 29/2011 አዳማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና፣ ደደቢት ከ መከላከያ፤ ጥር 30 ባህር ዳር ከነማ ከ ስሑል ሽረ፣ ጅማ አባ ጅፋር ከ ድሬዳዋ ከነማ፤ የካቲት 9 ጅማ አባ ጅፋር ከ ደደቢት፣ መከላከያ ከ ደሬዳዋ ከነማ፤ የካቲት 10 መቐለ 70 እንደርታ ከ ባህር ዳር ከነማ፤ የካቲት 13 ጅማ አባ ጅፋር ከ መከላከያ፤ የካቲት 17 ጅማ አባ ጅፋር ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም የካቲት 21 መቐለ 70 እንደርታ ከ ጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ፡፡

leave a reply