EthiopiaPoliticsSocial

አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በመጪው ቅዳሜ ጥዋት ወደ ኢትዮጵያ ይገባል፡፡

የአዲስ አበባ ብዙሃን መገናኛ እንደዘገበው የታማኝ በየነ ወደ ሀገሩ መመለስ ከግለሰብም በላይ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን እርሱን ለመቀበል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ገልጿል፡፡
አርቲስት ታማኝ በየነን ለመቀበል የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳለው ታማኝ በመጪው ቅዳሜ አዲስ አበባ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ይደረግለታል፡፡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ፣በብሄራዊ ትያትር ቤት እንዲሁም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖሩ መርሃ ግብሮች ላይ ንግግር ያደርጋልም ተብሏል፡፡
በመግለጫዉ የተገኙት የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንዳሉት አክቲቪሲስት ታማኝ በየነ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ዋሽንግተን በነበራቸዉ ቆይታ የጥላቻ ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ በሚል የያዙትን መልካም ተግባር ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ነሀሴ 27 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው መርሀ ግብር ከ25 ሺ በላይ የተለያዩ ታዳሚዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶችና ከፍተኛ ባለስልጣናት እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን በዝግጅቱ ለሚሳተፉ አካላት በተመረጡ የሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በ10ሩም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች መግቢያ በነፃ ማግኘት እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡
አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ ከአሜሪካም አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button