Regions

በኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ የትግይ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን

በኢትዮኤርትራ ግንኙነት ዳግም መጀመር የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል አሉ የትግይ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድር / ደብረጽዮን

ዶክተር ደብረፂዮን ይህን ያሉት የተጀመረውን የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ የሁለቱ ሀገራት አጎራባች ህዝቦች በሰቲት ሁመራ ተከዜ ወንዝ ድንበር ላይ በተደረገ ክብረበአል ላይ ነው፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ  ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንደተናገሩት፥ የተቋረጠው የሀገራቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጀመር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

ጨምረውም በኢትዮጵያ የትግራይ ምዕራባዊ ዞንና በኤርትራ ጋሽ ባርካ አጎራባች ህዝቦች ከእንግዲህ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት በማጠናክር ቀጣይ ጉዟቸውን ብሩህ ሊያደርጉ ይገባልም ብለዋል።

ለግንኙነቱ ቀጣይነትም የትግራይ ክልል አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ነው ምክትል ርእሰመስተዳድሩ የገለፁት፡፡

በተከዜ ወንዝ ዳርቻ በተካሔደው በዚህ ስነ-ስርዓት ላይ ዶክተር ደብረጽዮንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የጋሽ ባርካ ነዋሪዎችና ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶችና፣ የምዕራባዊ ትግራይ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል። መረጃውን ከትግራይ ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት አግኝተነዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button