COVID-19HealthNewsSocialኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1መቶ 16 ደረሰ ባጠቃላይ 21 ሰዎችም አገግመዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1መቶ 16 ደረሰ ባጠቃላይ 21 ሰዎችም አገግመዋል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት በ 1 ሺህ 73 ሰዎች ላይ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ በ2 ሰዎች ላይ መገኘቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸዉ ሁለቱም ኢትዮጵያዊያን ወንዶች ሲሆኑ፤ የ22 ዓመቱ ሰዉ በአፋር ክልል ገዋኔ ነዋሪና የዉጭሀገር የጉዞ ታሪክ የሌለዉ ሲሆን ጉዳዩ በመጣራት ላይ ነዉ፡፡ሁለተኛዉ የ54 ዓመት ሰዉ ከአሜሪካ የመጠና በለይቶ ማቆያ ዉስጥ የነበረ መሆኑ ታዉቋል፡፡
በ24 ሰዓታት ዉስጥ 5 ሰዎች ከበሽታዉ ያገገሙ ሲሆን ፤ባጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል፡፡

በጽኑ ህክምና ላይም ሚገኝ ታማሚ እንደሌለ ተገልጿል፡፡90 ሰዎች ደግሞ በፋይረሱ ተይዘዉ በለይቶ ህክምና ዉስጥ ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑን ከጤና ሚንስትሯ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ባጠቃላይ በኢትዮጵያ 9ሺህ 7መቶ 71 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸዉ ሲሆን አስካሁን ድረስም በበሽታዉ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 መቶ 16 ደርሷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button