Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮችን ሊያወያዩ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለተደረገው ሪፎርም ፣ ባለፉት 10 ወራት በተገኙ የዲፕሎማሲ ውጤቶች እና ቀጣይ የውጭ ጉዳይ ተልዕኮ ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ ጋር የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ይበልጥ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ፣ከዳያስፖራው ጋር ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገራቸው አምባሳደሮች ሆነው እንዲንቀሳቀሱ፣  የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲው በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይም ይወያያሉ ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

በውይይቱ አዳዲስ ተሿሚ እና ነባር አምባሳደሮችን ጨምሮ 60 የሚሲዮን መሪዎች እና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ይሳተፋሉ ተብሏል።

በተያያዘ ዜና ከዚህ ቀደም የውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በነበሩትና በአምባሳደርነት በተሾሙት  አቶ መለስ አለም ቦታ በአቶ ነብያት  ጌታቸው  መተካቱ ይፋ ሆኗል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button